ኢያሱ 14:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ሆነው ነበርና፤ ለሌዋውያኑ ግን ከሚኖሩባቸው ከተሞች እንዲሁም ለበግ፣ ለፍየልና ለከብት መንጎቻቸው መሰማሪያ እንዲሆን ዐብሮ የተከለለላቸውን ምድር ብቻ እንጂ ሌላ አልሰጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን ማሰማርያ በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም በምድሪቱ ለመኖሪያቸው የሚሆኑ ከተሞችና ለከብቶቻቸው ማሰማሪያ የሚሆን መሬት በቀር የርስት ድርሻ አልተሰጣቸውም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንስሶቻቸው ከሚሆን ማሰማሪያቸውና ከእንስሶቻቸውም በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፥ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። |
“ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ የወለድሃቸው ሁለቱ ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ሆነው ይቈጠራሉ፤ ሮቤልና ስምዖን ልጆቼ እንደ ሆኑ ሁሉ፣ ኤፍሬምና ምናሴም ልጆቼ ይሆናሉ።
ሕዝቅያስ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲመጡ፣ ለመላው እስራኤልና ለይሁዳ መልእክት ላከ፤ ለኤፍሬምና ለምናሴም ደብዳቤ ጻፈ።