ኢያሱ 10:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢያሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ኋላ ተመልሰው ዳቤርን ወጓት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ዳቤር ተመለሱ፥ እርሷንም ወጉአት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢያሱና ሠራዊቱ ወደ ደቢር ተመልሰው በመዝመት አደጋ ጣሉባት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም፥ ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ዳቤር ተመለሱ፤ ወጉአትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ዳቤር ተመለሱ፥ ወጉአትም፥ |
ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋራ ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ።
ከተማዪቱን፣ ንጉሧንና መንደሮቿን ይዘው በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ደመሰሱ፤ በልብናና በንጉሧ እንዲሁም በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ እዚህም በዳቤርና በንጉሧ ላይ ደገሙት።