La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮናስ 1:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱ አስቀድሞ ነግሯቸው ስለ ነበር፣ ከእግዚአብሔር እንደ ኰበለለ ዐወቁ፣ ስለዚህም በሁኔታው በመደንገጥ፣ “ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰዎቹም እጅግ ፈሩ፥ እንዲህም አሉት፦ “ይህ ያደረግኸው ምንድነው?” እርሱ ስለ ነገራቸው፥ ከጌታ ፊት እንደ ኰበለለ አውቀዋልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት የኰበለለ መሆኑን ዐወቁ፤ ስለዚህም በጣም ፈርተው “ይህን ያደረግኸው ለምንድን ነው?” አሉት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ኰበ​ለለ እርሱ ስለ ነገ​ራ​ቸው ዐው​ቀ​ዋ​ልና እጅግ ፈር​ተው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አሉት።

Ver Capítulo



ዮናስ 1:10
8 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላክ ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች።


ኢዮአብ ግን ንጉሡን፣ “አምላክህ እግዚአብሔር ሰራዊቱን በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ይብቃ፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።


ከነፋሱ ብርታት ለማምለጥ ይሮጣል፤ ነገር ግን እየተወረወረ ያለ ርኅራኄ ይደርስበታል፤


የባሕሩም ማዕበል እጅግ እየበረታ ስለ ሄደ፣ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት።


ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፤ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጕዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።


ጲላጦስ ይህን ሲሰማ የባሰውኑ ፈራ፤


ኢያሱም፣ “እንዲህ ያለውን መከራ ለምን አመጣብህን? እነሆ፤ ዛሬ በአንተም ላይ እግዚአብሔር መከራ ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤል በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤ የቀሩትንም እንደዚሁ ከወገሩ በኋላ በእሳት አቃጠሏቸው።