Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 24:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኢዮአብ ግን ንጉሡን፣ “አምላክህ እግዚአብሔር ሰራዊቱን በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ይብቃ፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢዮአብ ግን ንጉሡን፥ “ጌታ አምላክህ ሕዝቡን መቶ ዕጥፍ ያድርገው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ያብቃው፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮአብ ግን “ንጉሥ ሆይ! አምላክህ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ አሁን ካሉት ይልቅ በመቶ እጅ ያብዛልህ፤ ይህንንም ሲያደርግ ለማየት እንድትበቃ ዕድሜህን ያርዝምልህ፤ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! ይህን ለማድረግ ስለምን ፈለግኽ?” አለው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኢዮ​አ​ብም ንጉ​ሡን፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ዐይን እያየ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨ​ም​ር​በት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈ​ል​ጋል?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኢዮአብም ንጉሡን፦ የጌታዬ የንጉሡ ዓይን እያየ አምላክህ እግዚአብሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨምርበት፥ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይወድዳል? አለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 24:3
7 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሠኘውን ያድርግ።”


ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች ስላሸነፋቸው፣ የእስራኤልን ሰራዊት ለመመዝገብ ከፊቱ ወጥተው ሄዱ።


እግዚአብሔር እናንተንና ልጆቻችሁን፣ በባርኮቱ ያብዛችሁ።


የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ክብር ሲሆን፣ የዜጎች ማነስ ግን ለገዥ መጥፊያው ነው።


ከዚያም ታያለሽ፤ ታብረቀርቂአለሽ፤ ልብሽ ይዘልላል፤ በደስታም ይሞላል። በባሕሮች ያለው ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል፤ የነገሥታትም ብልጽግና የአንቺ ይሆናል።


አሁንም የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ሺሕ ጊዜ ያብዛችሁ፣ በሰጠውም ተስፋ መሠረት ይባርካችሁ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos