ኢዩኤል 1:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ለልጆቻችሁ ተናገሩ፤ ልጆቻችሁ ለልጆቻቸው ይንገሩ፤ ልጆቻቸውም ለሚቀጥለው ትውልድ ይንገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው፥ ልጆቻቸውም ለኋለኛው ትውልድ ይንገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ነገር ለልጆቻችሁ ንገሩ፤ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው ይንገሩ፤ እነርሱ ደግሞ ለሚከተለው ትውልድ ይንገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ለልጆቻችሁ ንገሩ፤ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው፥ ልጆቻቸውም ለኋለኛው ትውልድ ይንገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው፥ ልጆቻቸውም ለኋለኛው ትውልድ ይንገሩ። |
“በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ እንዲህ በለው፤ ‘ከባርነት ምድር ከግብጽ እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ አወጣን፤