Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዩኤል 1:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እናንተ ሽማግሌዎች፣ ይህን ስሙ፤ በምድሪቱም የምትኖሩ ሁላችሁ፣ አድምጡ፤ በእናንተ ዘመንም ሆነ በአባቶቻችሁ ዘመን፣ እንዲህ ዐይነት ነገር ሆኖ ያውቃልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እናንተ ሽማግሌዎች፥ ይህን ስሙ፤ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፥ አድምጡ። ይህ በዘመናችሁ ወይስ በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ነበርን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ! በይሁዳም ምድር የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! ለመሆኑ ይህን የመሰለ ነገር በዘመናችሁ ወይም በቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ተደርጎ ያውቃልን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እና​ንተ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች! ይህን ስሙ፤ በም​ድ​ርም የም​ት​ኖሩ ሁሉ አድ​ምጡ። ይህ በዘ​መ​ና​ችሁ ወይስ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ዘመን ሆኖ ነበ​ርን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እናንተ ሽማግሌዎች፥ ይህን ስሙ፥ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፥ አድምጡ። ይህ በዘመናችሁ ወይስ በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ነበርን?

Ver Capítulo Copiar




ኢዩኤል 1:2
24 Referencias Cruzadas  

ይህም የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። የንጋት ብርሃን በተራሮች ላይ እንደሚወጣ፣ ኀያልና ብዙ ሰራዊት ይመጣል፤ ከጥንት እንዲህ ዐይነት ከቶ አልነበረም፤ በሚመጡትም ዘመናት እንዲህ ዐይነት ከቶ አይሆንም።


“እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት፤ አስተውሉ! የንጉሥ ቤት ሆይ፤ አድምጡ! ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።


ወዮ ለዚያ ቀን! እንደዚያም ያለ አይኖርም፤ ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤ ነገር ግን ይተርፋል።


“የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፤ አባቶቻቸውም የደረሱበትን መርምረህ አግኝ፤


በዚያ ጊዜ፣ ከዓለም መጀመሪያ እስከ ዛሬ ድረስ ሆኖ የማያውቅ፣ ከዚህም በኋላ ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል።


ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”


እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣ እናንተ የእስራኤል ቤት ገዦች፣ ፍትሕን የምትንቁ፣ ትክክለኛ የሆነውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፤ ስሙ፤


ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎች፤ እናንተ የእስራኤል ቤት ገዦች ስሙ፤ ፍትሕን ማወቅ አይገባችሁምን?


እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤ ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤ ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ ልዑል እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይመሰክርባችኋል።


የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤


እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤


የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብጽ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤


ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤ የተቀደሰንም ጉባኤ ጥሩ፤ ሽማግሌዎችን ሰብስቡ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ጥሩ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።


እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።


“በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያ ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ።


እናንተ ዐይን እያላችሁ የማታዩ፣ ጆሮ እያላችሁ የማትሰሙ፣ ሞኞችና የማታስተውሉ ሰዎች ይህን ስሙ፤


እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ኑ አድምጡም፤ እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አስተውሉ። ምድርና በውስጧ ያለ ሁሉ፣ ዓለምና ከርሷ የሚበቅል ሁሉ ይስማ!


ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው።”


እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ።


ኀጢአተኞች ለምን በሕይወት ይኖራሉ? ለምን ለእርጅና ይበቃሉ? ለምንስ እያየሉ ይሄዳሉ?


በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡ፣ የሸበቱ ሽማግሌዎች ከእኛ ጋራ አሉ።


ጥበብ ያለው በአረጋውያን ዘንድ አይደለምን? ማስተዋልስ ረዥም ዕድሜ ባላቸው ዘንድ አይገኝምን?


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን፣ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ አደርገዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios