ስለዚህ የባቢሎናውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠው።
ኤርምያስ 9:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞት በመስኮቶቻችን ገብቷል፤ ወደ ምሽጎቻችንም ዘልቋል፤ ሕፃናትን ከየመንገዱ፣ ወጣቶችን ከየአደባባዩ ጠራርጎ ወስዷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃናቱን ከመንገድ ጉልማሶቹንም ከአደባባይ ለማጥፋት ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ ንጉሥ ቅጥሮቻችን ውስጥ ገብቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞት በየመስኮቶቻችን ገብቶአል፤ በየቤተ መንግሥታችንም ውስጥ ገብቷል፤ ልጆችን በየመንገዱ፥ ጐልማሶችንም በየአደባባዩ ቀሥፎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃናቱንም በመንገድ፤ ጐልማሶቹንም በአደባባዮቻችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመስኮቶቻችን ወደ ሀገራችን ገብቶአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃናቱን ከመንገድ ጕልማሶቹንም ከአደባባይ ያጠፉ ዘንድ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል። |
ስለዚህ የባቢሎናውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠው።
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣ ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤ ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤ ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤ ጕልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።
“አሁንም የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ዘር እንዳይቀርላችሁ ወንዶችና ሴቶች፣ ልጆችና ሕፃናት በይሁዳ እንዳይገኙ ለምን እንዲህ ዐይነት ታላቅ ጥፋት በራሳችሁ ላይ ታመጣላችሁ?
በእነርሱ ላይ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፤ በውስጤም ልይዘው አልቻልሁም። “መንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናት፣ በተሰበሰቡ ወጣቶችም ላይ አፍስሰው፤ ባልም ሚስትም፣ ያረጁና የጃጁም አያመልጡም።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክልን አስቀምጣለሁ፤ አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድነት ይደናቀፉበታል፤ ጎረቤቶችና ባልንጀሮችም ይጠፋሉ።”
በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን እንደ ተጣለ ጕድፍ በምድር ላይ ይበተናል።
“እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣ በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና። ደማቸው እንደ ትቢያ፣ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይጣላል።