ኤርምያስ 9:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ፈጥነው ይምጡ፤ ዐይኖቻችን እንባ እስኪያጐርፉ፣ ሽፋሽፍቶቻችንም ውሃ እስኪያመነጩ፣ ስለ እኛ ሙሾ ያውርዱልን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ያነሳሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም እንዲህ አሉ፦ “ዐይናችን በእንባ እንዲርስ፥ በጉንጫችንም እንባው እንዲወርድ፥ አስለቃሾች በቶሎ ሙሾ እንዲያወጡ ንገሩአቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጥነውም ሙሾ ያሙሹላችሁ፤ ዐይኖቻችሁም እንባን ያፍስሱ፤ ከዐይኖቻችሁም ሽፋሽፍቶች ውኃ ይፍለቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ይያዙ። |
ባትሰሙ ግን፣ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኳልና፣ ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤ እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።
“ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ “ ‘ድንግሊቱ ልጄ፣ ሕዝቤ፣ በታላቅ ስብራት፣ በብርቱ ቍስል ተመትታለችና ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት፣ ሳያቋርጡ እንባ ያፈስሳሉ
እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።
“ ‘እግዚአብሔር ቍጣው የወረደበትን ይህን ትውልድ ስለ ናቀውና ስለ ተወው፣ ጠጕርሽን ቈርጠሽ ጣዪ፤ በባድሞቹ ኰረብቶች ላይ ሆነሽም ሙሾ አውጪ።
ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች ዐዝናለሁ። ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤ የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤ የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤ የዱር አራዊትም ጠፍተዋል።
እናንተ ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣ አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።
በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጕንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣ የሚያጽናናት ማንም የለም፤ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላቶቿም ሆነዋል።
ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣ በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።
የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ? ከምንስ ጋራ አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አጽናናሽ ዘንድ፣ በምን ልመስልሽ እችላለሁ? ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤ ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል?
የሕዝቡ ልብ፣ ወደ ጌታ ጮኸ። የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፤ ቀንና ሌሊት፣ እንባሽ እንደ ወንዝ ይፍሰስ፤ ለራስሽ ዕረፍትን አትስጪ፣ ዐይኖችሽ ከማንባት አያቋርጡ።
ስለዚህ ጌታ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በየመንገዱ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤ በአደባባዩም የሥቃይ ጩኸት ይሆናል፤ ገበሬዎች ለልቅሶ፣ አልቃሾችም ለዋይታ ይጠራሉ።