ኤርምያስ 6:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ንቋቸዋልና፣ የተናቀ ብር ተብለው ይጠራሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ጥሎአቸዋልና ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሩአቸዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር ስለ ጣልኳቸው ‘ንጹሕ ባለመሆኑ የወደቀ ብር’ ብለው ይጠሩአቸዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና የተናቀ ብር ብላችሁ ጥሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ጥሎአቸዋልና የተጣለ ብር ብለው ይጠሩአቸዋል። |
የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ፣ ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤ እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው።
ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ተጸየፈቻትን? ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ፣ ለምን ክፉኛ መታኸን? ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም በጎ ነገር አላገኘንም፤ የፈውስን ጊዜ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነ።
“ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፣ ‘የእግዚአብሔር ሸክም ምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቁ፣ ‘ሸክሙ እናንተ ናችሁ፤ እወረውራችኋለሁ’ ይላል እግዚአብሔር ብለህ መልስላቸው።
“ ‘እግዚአብሔር ቍጣው የወረደበትን ይህን ትውልድ ስለ ናቀውና ስለ ተወው፣ ጠጕርሽን ቈርጠሽ ጣዪ፤ በባድሞቹ ኰረብቶች ላይ ሆነሽም ሙሾ አውጪ።
“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም።
እንግዲህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተዋቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ ከቶ አይሆንም! እኔ ራሴ ከብንያም ነገድ፣ የአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ።