ታበጥራቸዋለህ፤ ነፋስ ጠርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል። አንተ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእስራኤል ቅዱስ ሞገስ ታገኛለህ።
ኤርምያስ 51:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲያበጥሯትና እንዲያወድሟት፣ ባዕዳንን በባቢሎን ላይ እልካለሁ፤ በመከራዋም ቀን፣ ከብበው ያስጨንቋታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባቢሎንም ላይ የሚያዘሩትን ሰዎች እልካለሁ እነርሱም ያዘሩአታል፥ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፤ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እንደ እህል የሚያበጥሯትና ምድርዋን የሚያጠፉ የውጪ ጠላቶችን ወደ ባቢሎን እልካለሁ፤ እነርሱም የምትጠፉበት ጊዜ ሲደርስ ከየአቅጣጫው አደጋ ይጥሉባታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባቢሎንም ላይ ተሳዳቢ ሰዎችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ይሰድቧታል፤ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፤ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባቢሎንም ላይ የሚያዘሩትን ሰዎች እሰድዳለሁ እነርሱም ያዘሩአታል፥ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፥ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል። |
ታበጥራቸዋለህ፤ ነፋስ ጠርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል። አንተ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእስራኤል ቅዱስ ሞገስ ታገኛለህ።
የእስራኤል ቅዱስ፣ የሚቤዣችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ ሰራዊት እሰድዳለሁ፤ በሚመኩባቸውም መርከቦች፣ ባቢሎናውያንን ሁሉ እንደ ኰብላይ አመጣለሁ።
“ቀስት የሚገትሩትን፣ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ፣ ዙሪያውን ሁሉ መሽጉ፤ የእስራኤልን ቅዱስ፣ እግዚአብሔርን አቃልላለችና፣ እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ በሌሎች ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።
ከሕዝብሽ ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፤ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፤ ሌላው ሢሶ ከቅጥርሽ ውጪ በሰይፍ ይወድቃል፤ የቀረውን ሢሶ ደግሞ ለነፋስ እበትናለሁ፤ በተመዘዘም ሰይፍ አሳድደዋለሁ።