Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 51:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ ተሳ​ዳቢ ሰዎ​ችን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ድ​ቧ​ታል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባዶ ያደ​ር​ጋሉ፤ በመ​ከ​ራም ቀን በዙ​ሪ​ያዋ ይከ​ብ​ቡ​አ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንዲያበጥሯትና እንዲያወድሟት፣ ባዕዳንን በባቢሎን ላይ እልካለሁ፤ በመከራዋም ቀን፣ ከብበው ያስጨንቋታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በባቢሎንም ላይ የሚያዘሩትን ሰዎች እልካለሁ እነርሱም ያዘሩአታል፥ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፤ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔ እንደ እህል የሚያበጥሯትና ምድርዋን የሚያጠፉ የውጪ ጠላቶችን ወደ ባቢሎን እልካለሁ፤ እነርሱም የምትጠፉበት ጊዜ ሲደርስ ከየአቅጣጫው አደጋ ይጥሉባታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በባቢሎንም ላይ የሚያዘሩትን ሰዎች እሰድዳለሁ እነርሱም ያዘሩአታል፥ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፥ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 51:2
9 Referencias Cruzadas  

ታበ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ነፋ​ስም ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ ዐውሎ ነፋ​ስም ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ደስ ይል​ሃል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ የሚ​ቤ​ዣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ እና​ንተ ወደ ባቢ​ሎን ሰድ​ጃ​ለሁ፤ ስደ​ተ​ኞ​ችን አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በመ​ር​ከብ ውስጥ ይታ​ሰ​ራሉ።


ሕዝ​ቤ​ንም ወደ ዳርቻ ፈጽሜ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የወ​ላድ መካን አድ​ር​ጌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤ​ንም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው አጥ​ፍ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አል​ተ​መ​ለ​ሱም።


“ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት።


አንቺ ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ!፥ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለ​ሽም፤ የሚ​ያ​ነ​ሳ​ሽም የለም፤ በዛ​ፎ​ችሽ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያሽ ያለ​ው​ንም ሁሉ ትበ​ላ​ለች።”


ከአ​ን​ቺም ሢሶው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በራብ ያል​ቃል፤ ሢሶ​ውም በዙ​ሪ​ያሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos