ኤርምያስ 49:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ በሸለቆችሽ ለምን ትመኪያለሽ? ለምንስ በፍሬያማ ሸለቆሽ ትኵራሪያለሽ? በብልጽግናሽ ተማምነሽ፣ ‘ማን ሊነካኝ ይችላል?’ ትያለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማን በእኔ ላይ ይመጣብኛል ብለሽ በመዝገብሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! በሸለቆችሽ፥ ውኃ በሚፈስስባቸው ሸለቆችሽ፥ ለምን ትመኪያለሽ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እየቀነሰ በሚሄደው ኀይላችሁ የምትመኩት ለምንድን ነው? እናንተ እምነተቢስ ሕዝብ ሆይ! ‘አደጋ የሚጥልብኝ ማነው?’ ብላችሁ በሀብታችሁ ክምችት ተመክታችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማን ይመጣብኛል ብለሽ በሀብትሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! በጠፉ ሸለቆዎችሽ ስለ ምን ትመኪያለሽ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማን ይመጣብኛል ብለሽ በመዝገብሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፥ በሸለቆችሽ፥ ውኃ በሚያረካቸው ሸለቆችሽ፥ ስለ ምን ትመኪያለሽ? |
ከሸለቆው በላይ፣ በድንጋያማው ዐምባ ላይ የምትኖሪ ሆይ፤ እኔ በአንቺ ላይ ወጥቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። “ማን በእኛ ላይ ይወጣል? ማንስ ወደ መኖሪያችን ደፍሮ ይገባል?” የምትሉ ሆይ፤
“ከዳተኛ ልጆች ሆይ፤ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድ ሁለት መርጫችሁ ወደ ጽዮን አመጣችኋለሁ።
አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ይፈጥራል፤ ሴት በወንድ ላይ ከበባ ታደርጋለች።”
አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤ የምትነዛው ሽብር፣ የልብህም ኵራት አታልሎሃል፤ መኖሪያህን እስከ ንስር ከፍታ ቦታ ብትሠራም፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።
እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብ ብለው ለማድመጥም አልፈለጉም፤ ይልቁን የክፉ ልባቸውን ሐሳብ በእልኸኝነት ተከተሉ፤ ወደ ፊት በመሄድ ፈንታም ወደ ኋላቸው ተመለሱ።
እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣ እልኸኞች ናቸው፤ ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶች እንዴት ያሰማራቸዋል?
በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
ለራሷ ክብርና ምቾት የሰጠችውን ያህል፣ ሥቃይና ሐዘን ስጧት፤ በልቧም እንዲህ እያለች ትመካለች፤ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ከቶም አላዝንም፤’