ኤርምያስ 39:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ የባቢሎናውያንም ሰራዊት ግን ተከትሎ አሳደዳቸው፣ በኢያሪኮም ሜዳ ደርሶባቸው ሴዴቅያስን ያዘ፤ ማርከውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ በዚያም የባቢሎን ንጉሥ ፈረደበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፥ በኢያሪኮም ሜዳ ሴዴቅያስን ደረሱበት፤ እርሱንም ይዘው በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የባቢሎን ሠራዊት ከኋላቸው ተከትሎ በማሳደድ በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ ደረሱበትና ሴዴቅያስን ማረኩት፤ ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሥ ናቡከደነፆር አመጡት፤ በዚያን ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር በሐማት ግዛት ሪብላ ተብላ በምትጠራ ከተማ ውስጥ ነበር፤ ንጉሥ ናቡከደነፆርም እዚያው በሴዴቅያስ ላይ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ ሜዳ አገኙት፤ ይዘውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ዴብላታ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፥ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ ሜዳ አገኙት፥ ይዘውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፥ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ። |
የአሦርም ንጉሥ ሕዝቡን ከባቢሎን፣ ከኩታ፣ ከአዋና ከሐማት፣ ከሴፈርዋይም ከተሞች አምጥቶ በእስራኤላውያን ቦታ እንዲገቡ በሰማርያ ከተሞች አሰፈራቸው፤ እነርሱም ሰማርያን ወርሰው በከተሞቿ ይኖሩ ጀመር።
በኢየሩሳሌም ተቀምጦ እንዳይገዛም ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ቦታ አሰረው፤ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት።
ስለዚህ እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሰራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ እነርሱም በምናሴ አፍንጫ መንጠቆ አገቡበት፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤ ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤ ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣ ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል።
ከዚያ በኋላ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን፣ ከመቅሠፍት፣ በከተማው ከሰይፍና ከራብ የተረፈውንም ሕዝብ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ሕይወታቸውን ለማጥፋት ለሚሹ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፤ አይራራላቸውም፤ አይምራቸውምም።’
“ ‘ነገር ግን ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበላ እንደማይቻለው እንደ መጥፎ በለስ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና ባለሥልጣኖቹን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የቀሩትንም ሆነ በግብጽ የሚኖሩትን፣ እንዲሁ አደርግባቸዋለሁ።
ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ባትሰጥ ግን ይህች ከተማ ለባቢሎናውያን ዐልፋ ትሰጣለች፤ እነርሱም ያቃጥሏታል፤ አንተም ራስህ ከእጃቸው አታመልጥም።’ ”
“ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ተወስደው ለባቢሎናውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ራስህ በባቢሎን ንጉሥ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ሊገድለው ለፈለገው ጠላቱ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፣ እንዲሁ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ሊገድሉት ለሚፈልጉ ጠላቶቹ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።’ ”
በመከራና በመረገጥ ብዛት ይሁዳ ተማርካ ሄደች፤ በሕዝቦችም መካከል ተቀመጠች፤ የምታርፍበትንም ስፍራ ዐጣች፤ በጭንቀቷ መካከል ሳለች፣ አሳዳጆቿ ሁሉ አገኟት።
እነርሱም የጦር መሣሪያ፣ ሠረገላና ጋሪ በመያዝ ብዙ ሕዝብ ሆነው ይመጡብሻል፤ ትላልቅና መለስተኛ ጋሻ በማንገብና የራስ ቍር በመድፋት በየአቅጣጫው ይሰለፉብሻል፤ እኔም ለፍርድ በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ በሕጋቸውም መሠረት ይቀጡሻል።
የጌባላውያንም ምድር፤ በምሥራቅም ከበኣልጋድ አንሥቶ በአርሞንዔም ተራራ ግርጌ ዐልፎ፣ እስከ ሐማት መተላለፊያ ያለው የሊባኖስ ምድር ሁሉ ነው።
እነዚህም አሕዛብ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፣ ከነዓናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ።