እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
ኤርምያስ 12:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣ አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው። የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል? |
እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ እኛም በዚህ ዕለት ተርፈን በሕይወት አለን። እነሆ፣ በፊትህ ከነበደላችን ቀርበናል፤ ከበደላችን የተነሣ ግን በፊትህ ሊቆም የሚችል ማንም የለም።”
በምድር ላይ የሚከሠት ሌላም ከንቱ ነገር አለ፤ ጻድቃን ለክፉዎች የሚገባውን፣ ክፉ ሰዎችም ለጻድቃን የሚገባውን ይቀበላሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ነው አልሁ።
አልሰማህም ወይም አላወቅህም፤ ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤ አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።
ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ በጽድቅም የምትፈርድ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን ላንተ ትቻለሁና፤ በእነርሱ ላይ የምትፈጽመውን በቀል ልይ።
“እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔ ግን በትእዛዙ ላይ ዐመፅ አድርጌ ነበር፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ወይዛዝርቶቼና ጐበዛዝቴ፣ ተማርከው ሄደዋል።
“እናንተ ግን፣ ‘የጌታ መንገድ ቀና አይደለችም’ ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስማ፤ መንገዴ ቀና አይደለችምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?
“ጌታ ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ለአንተ ባለመታመናችን እኛን በበተንህባቸው አገሮች ሁሉ የምንገኝ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምና የመላው እስራኤል ሕዝብ፣ በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለን በዚህ ቀን በኀፍረት ተከናንበናል።
በርሷ ውስጥ ያለው እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ አይሳሳትም፤ በየማለዳው ቅን ፍርድ ይሰጣል፤ በየቀኑም አይደክምም፤ ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም።
እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችሁታል። እናንተም፣ “ያታከትነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ? “ክፉ የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነው፤ እርሱም በክፉዎች ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ ወዴት ነው?” በማለታችሁ ነው።