ኤርምያስ 11:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ የተዋበ ፍሬ ያላት፣ የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎሽ ነበር፤ አሁን ግን በታላቅ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ፣ እሳት ያነድድባታል፤ ቅርንጫፎቿ ይሰባበራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ስምሽን፦ “በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ” ብሎ ጠራው፤ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ጊዜ እናንተ በፍሬ እንደ ተመላ የወይራ ዛፍ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንደ ነጐድጓድ የሚያስተጋባ ድምፅ በማሰማት ቅጠሉን በእሳት አቃጥላለሁ ቅርንጫፎችንም እሰባብራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ስምሽን፦ በመልካም ፍሬ የተዋበችና የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፤ ከመቈረጥዋም ድምፅ የተነሣ በላይዋ እሳት ነደደባት፤ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ስምሽን፦ በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፥ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። |
እኔ፣ እንደ ምርጥ የወይን ተክል፣ ጤናማና አስተማማኝ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ ታዲያ ብልሹ የዱር ወይን ተክል ሆነሽ፣ እንዴት ተለወጥሽብኝ?
“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ በሰውና በእንስሳ ላይ፣ በዱር ዛፍና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።