La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 49:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፥ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፥ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፥ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤ ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥ ወደ ዋሻው ይመለሳል፤ እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤ ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይሁዳ የአ​ን​በሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያህ ወጣህ፤ እንደ አን​በሳ ተኛህ፤ አን​ቀ​ላ​ፋ​ህም፤ እንደ አን​በ​ሳም ደቦል የሚ​ቀ​ሰ​ቅ​ስህ የለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ ከአደንህ ወጣሁ እንደ አንበሳ አሸመቀ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፤ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 49:9
11 Referencias Cruzadas  

በስድስቱም ደረጃዎች ጫፍ ላይ ግራና ቀኝ ዐሥራ ሁለት አንበሶች ቆመዋል። ይህን የመሰለ ዙፋን በማንኛውም አገር መንግሥት ተሠርቶ አያውቅም።


ዙፋኑ ባለስድስት ደረጃ ሲሆን፣ ከዙፋኑ ጋራ የተያያዘ ከወርቅ የተሠራ የእግር መርገጫ ነበረው። መቀመጫውም ግራና ቀኙ መደገፊያ ያለው ሲሆን፣ በመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመዋል።


“ ‘ተስፋዋ መጨናገፉን፣ የጠበቀችውም አለመሳካቱን ባየች ጊዜ፣ ከግልገሎቿ ሌላውን ወስዳ፣ ብርቱ አንበሳ አድርጋ አሳደገችው።


እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።


“የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም።


በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣ የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣ በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣ እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣ የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።


ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤ ያደነውን እስኪያነክት፣ የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣ እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።”


እንደ አንበሳ አድፍጠዋል፤ እንደ እንስቲቱም አንበሳ አድብተዋል፤ ሊቀሰቅሳቸውስ የሚችል ማን ነው? “የሚባርኩህ ቡሩክ፣ የሚረግሙህም ርጉም ይሁኑ።”


ከዚያም ግዛትን፣ ሥልጣንና ኀይልን ሁሉ ከደመሰሰ በኋላ መንግሥትን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ፣ ያን ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል፤


ስለ ጋድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተመሰገነ ነው! ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፣ ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል።


ከዚያም ከሽማግሌዎቹ አንዱ፣ “አታልቅስ፤ እነሆ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፣ የዳዊት ሥር ድል ነሥቷል፤ እርሱ መጽሐፉን ሊከፍትና ሰባቱንም ማኅተሞች ሊፈታ ይችላል” አለኝ።