ዘፍጥረት 20:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አቢሜሌክ፣ “ለመሆኑ ይህን ያደረግህበት ምክንያት ምንድን ነው?” ሲል አብርሃምን ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሜሌክም አብርሃምን አለው፦ ይህን ማድረግህ ምን አይተህ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ይህን ያደረግኸው ለምንድን ነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም አብርሃምን አለው፥ “ይህን ነገር ማድረግህ ምን አይተህ ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክም አብርሃምን አለው፤ ይህን ማድረግህ ምን አይተህ ነው? |
አብርሃምም አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ ‘እዚህ ቦታ ፈሪሀ እግዚአብሔር አለመኖሩን ተገነዘብሁ፤ ሰዎቹም ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል’ ብዬ ሠጋሁ፤
ከዚያም አቢሜሌክ አብርሃምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? ምን በደልሁህና ነው በእኔና በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ታላቅ የጥፋት መዘዝ ያመጣህብን? በእውነቱ መደረግ የማይገባውን ነው ያደረግህብን።”