“ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነውን ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናደርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው?
ዘዳግም 8:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ እንዲህ ያለች መልካም ምድር ስለ ሰጠህ አምላክህን እግዚአብሔርን ባርከው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ፥ ስለሰጠህም ስለመልካሚቱ ምድር ጌታን አምላክህን ትባርካለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በልተህ ትጠግባለህ፤ ይህችን ለም ምድር የሰጠህን እግዚአብሔር አምላክህንም ታመሰግናለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትበላማለህ፤ ትጠግብማለህ፤ ስለ ሰጠህም ስለ መልካሚቱ ምድር አምላክህን እግዚአብሔርን ታመሰግናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ፥ ስለሰጠህም ስለመልካሚቱ ምድር አምላክህን እግዚአብሔርን ትባርካለህ። |
“ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነውን ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናደርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው?
እስክትጠግቡ የምትበሉት ብዙ ምግብ ይኖራችኋል፤ ድንቅ ነገሮችን ለእናንተ የሠራውን፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም።
ከዚያም ሕዝቡ በሣሩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ ዐምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ዐይኑን ወደ ሰማይ በማቅናት አመስግኖና ባርኮ እንጀራውን ቈረሰ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሰጠ፤ እነርሱም ለሕዝቡ ሰጡ።
አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው፣ እንዲህ የሚያደርገው ለጌታ ብሎ ነው፤ ሥጋ የሚበላውም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባልና። የማይበላም ለጌታ ሲል አይበላም፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርባል።
ወተትና ማር ወደምታፈስሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ባመጣኋቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፣ ከበለጸጉም በኋላ፣ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።