Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዩኤል 2:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እስክትጠግቡ የምትበሉት ብዙ ምግብ ይኖራችኋል፤ ድንቅ ነገሮችን ለእናንተ የሠራውን፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የጌታ የአምላካችሁን ስም ታመሰግናላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ብዙ በልታችሁ ትጠግባላችሁ፤ ብዙ አስደናቂ ነገር ያደረግኹላችሁን እኔን እግዚአብሔር አምላካችሁን ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ኀፍረት አይደርስባቸውም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ብዙ መብል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጠ​ግ​ቡ​ማ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተአ​ም​ራ​ትን የሠ​ራ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ታመ​ሰ​ግ​ና​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዩኤል 2:26
41 Referencias Cruzadas  

መጽሐፍ እንደሚለው፣ “በርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።”


ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!


ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሷልና።


በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትበላላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን በባረከበት፣ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተ ሰዎችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።


ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ፣ እቴጌዎቻቸው ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽን ትቢያ ይልሳሉ፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔን ተስፋ የሚያደርጉም አያፍሩም።”


እስራኤል ግን በእግዚአብሔር፣ በዘላለም ድነት ይድናል፤ እናንተም ለዘላለም፣ አታፍሩም፤ አትዋረዱም።


የምትወቁት እህል፣ የወይን ዘለላ እስከምትቈርጡበት ጊዜ፣ የምትቈርጡትም የወይን ዘለላ፣ እህል እስከምትዘሩበት ጊዜ ያደርሷችኋል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ላይ ያለ ሥጋት ትኖራላችሁ።


እንግዲህ ልጆች ሆይ፤ እርሱ ሲገለጥ ድፍረት እንዲኖረን፣ በሚመጣበትም ጊዜ በፊቱ እንዳናፍር በርሱ ኑሩ።


ይህም፣ “እነሆ፤ የሚያደናቅፍ ድንጋይ፣ የሚጥልም ዐለት፣ በጽዮን አስቀምጣለሁ፤ በርሱም የሚያምን አያፍርም” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።


“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።


እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፣ ድንቅ ነገር፣ በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና።


እንዴት ውብና አስደናቂ ይሆናሉ፤ እህል ጕልማሶችን፣ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅትን ያሳምራል።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ይከልላቸዋል፤ ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጣሉ፤ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የመሠዊያውን ማእዘኖች ለመርጨት፣ እንደ ተዘጋጀ ዕቃ፣ እነርሱም እንደዚሁ ተሞልተዋል።


በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ፣ በዚያ ቀን አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን፣ ከዚህች ከተማ አስወግዳለሁና፤ ከእንግዲህ ወዲያ፣ በቅዱስ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም።


ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔር ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤ “ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም።


እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብሁልህን ስጦታዬን እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለ ለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ።


በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጕልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።


እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋራ ሰብስቤአለሁ፤ የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ። ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንተ ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ።


ጻድቅ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ የክፉዎች ሆድ ግን እንደ ተራበ ይኖራል።


ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና።


ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።


ብቻውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።


በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤ በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።


ቸርነቱ ታምኛለሁና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።


የተመሸጉ ከተሞቻቸውንና የሠባውን ምድር ያዙ፤ በመልካም ነገር ሁሉ የተሞሉ ቤቶቻቸውን፣ የተቈፈሩ የውሃ ጕድጓዶቻቸውን፣ የወይን ተክላቸውን፣ የወይራ ዛፎቻቸውንና ስፍር ቍጥር የሌላቸውን የፍሬ ዛፎች ያዙ። እስኪጠግቡ በሉ፤ ወፈሩም፤ በታላቅ በጎነትህም ደስ ተሠኙ።


አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፣ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፣ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል።


እዚያም እናንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁ፣ እንዲሁም የራሳቸው ድርሻ ወይም ርስት የሌላቸው በየከተሞቻችሁ የሚኖሩት ሌዋውያን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ሐሤት አድርጉ።


በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ እንዲህ ያለች መልካም ምድር ስለ ሰጠህ አምላክህን እግዚአብሔርን ባርከው።


የእንጀራችሁ እህል እንዲቋረጥ በማደርግበት ጊዜ፣ ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ላይ እንጀራ ይጋግራሉ፤ እንጀራውንም በሚዛን መዝነው እናንተም ትበላላችሁ፤ ግን አትጠግቡም።


ትበላለህ፤ ነገር ግን አትጠግብም፤ ሆድህ እንዳለ ባዶውን ይቀራል፤ ታከማቻለህ፤ ነገር ግን አይጠራቀምልህም፤ የሰበሰብኸውን ለሰይፍ አደርገዋለሁና።


በሜዳ ላይ ለከብቶችህ ሣር እሰጣለሁ፤ አንተም ትበላለህ፤ ትጠግባለህም።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።


ምድሪቱ ፍሬዋን ትሰጣለች፤ እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤ በዚያም ያለ ሥጋት ትኖራላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios