ታዲያ ለእነርሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም እንዲሆንላቸው፣ እኔን እንዲፈሩና ሁልጊዜ ትእዛዞቼን ሁሉ እንዲጠብቁ እንደዚህ ያለ ልብ ቢኖራቸው ምናለ!
ዘዳግም 5:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሄደህ ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ ንገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ሂድና፦ “ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ” ብለህ ንገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም ሂድና ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ ንገራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄደህ፦ ወደ ቤቶቻችሁ ተመለሱ በላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄደህ፦ ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ በላቸው። |
ታዲያ ለእነርሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም እንዲሆንላቸው፣ እኔን እንዲፈሩና ሁልጊዜ ትእዛዞቼን ሁሉ እንዲጠብቁ እንደዚህ ያለ ልብ ቢኖራቸው ምናለ!
አንተ ግን እንዲወርሷት በምሰጣቸው ምድር እንዲጠብቋቸው የምታስተምራቸውን ትእዛዞች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች ሁሉ እንድሰጥህ እዚሁ ከእኔ ዘንድ ቈይ።”