እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ መሪያችንም እርሱ ነው። መለከት የያዙ ካህናቱም የጦርነቱን ድምፅ በእናንተ ላይ ያሰማሉ። እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ አይቀናችሁምና፣ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ አትዋጉ።”
ዘዳግም 3:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር ራሱ ይዋጋላችኋልና አትፍሯቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላካችሁ እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋልና አትፍሯቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚዋጋላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ ሆነ እነርሱን አትፍሩ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋልና ከእነርሱ የተነሣ አትፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋልና አትፍራቸውም ብዬ አዘዝሁት። |
እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ መሪያችንም እርሱ ነው። መለከት የያዙ ካህናቱም የጦርነቱን ድምፅ በእናንተ ላይ ያሰማሉ። እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ አይቀናችሁምና፣ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ አትዋጉ።”
ይህን ጦርነት የምትዋጉት እናንተ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁንም ማዳን እዩ። አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገውኑ ውጡና ግጠሟቸው፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋራ ይሆናል።’ ”
ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤ አንተ ወድደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።
መንዳት እንዳይችሉም የሠረገላዎቹን መሽከርከሪያዎች አቈላለፈባቸው፤ ግብጻውያኑም፣ “ከእስራኤላውያን እንሽሽ! እግዚአብሔር ግብጽን እየተዋጋላቸው ነው” አሉ።
እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እርሱን ከመላው ሰራዊቱና ከምድሩ ጋራ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን ሁሉ በርሱም ላይ አድርግበት” አለው።
ጠላቶችህን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄድ፣ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ከአንተ የሚበልጥ ሰራዊትንም በምታይበት ጊዜ አትፍራቸው፤ ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነውና።
በዚያ ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ስል አዘዝሁት፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አሁንም ዐልፈህ በምትሄድባቸው መንግሥታት ላይ ሁሉ እግዚአብሔር ይህንኑ ይደግመዋል።
ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን ያሸነፈው በአንድ ዘመቻ ብቻ ነበር፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተዋግቶላቸዋልና።