እነሆ ቤተ ዘመዱ ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሥተው፣ ‘ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለንና ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፣ ከዚያም ወራሽ አልባ ትሆኛለሽ’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”
2 ሳሙኤል 21:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፣ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋራ ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የጸሩያ ልጅ አቢሳ ዳዊትን ለመርዳት መጥቶ በዚያ ኀያል ሰው ላይ አደጋ በመጣል ገደለው፤ ከዚያን በኋላ የዳዊት ተከታዮች ዳግመኛ ከእነርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄድ ዳዊትን ቃል በማስገባት “የእስራኤል መብራት የሆንክ አንተ እንዳትጠፋ ዳግመኛ ወደ ጦርነት አትወጣም” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽሩያም ልጅ አቢሳ አዳነው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፦ አንተ የእስራኤልን መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም ብለው ማሉለት። |
እነሆ ቤተ ዘመዱ ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሥተው፣ ‘ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለንና ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፣ ከዚያም ወራሽ አልባ ትሆኛለሽ’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”
ዳዊትም ሰራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጋታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሰራዊቱ፣ “እኔ ራሴም ዐብሬአችሁ በርግጥ እወጣለሁ” አላቸው።
ሰዎቹ ግን፣ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፣ ሰዎቹ ከቁም ነገር አይቈጥሩንም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት ደንታቸው አይደለም፣ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺሕ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት።
ስሜ እንዲኖርባት በመረጥኋት በዚያች በኢየሩሳሌም ከተማ ለባሪያዬ ለዳዊት ምን ጊዜም በፊቴ መብራት እንዲኖረው፣ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጣለሁ።
የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ “ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሄጄ ልግደለው፤ ሸሽተው ወደ አንተ የመጡት አይሁድ እንዲበተኑ፣ በይሁዳም የቀሩት እንዲጠፉ ለምን ይገድልሃል?” ብሎ በምጽጳ ለጎዶልያስ በምስጢር ነገረው።