1 ሳሙኤል 2:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ጋራ የሚጣሉ ይደቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል። “ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፥ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፥ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል። |
“አሁንም ባሪያዬ ዳዊትን እንዲህ በለው፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ፤
አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣ አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በነጐድጓድ፣ በምድር መናወጥና በታላቅ ድምፅ፣ በዐውሎ ነፋስና በኀይለኛ ሞገድ፣ ፈጽሞ በሚባላም የእሳት ነበልባል ይመጣል።
“በዚያ ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ፤
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።
በእውነትም ሄሮድስና ጳንጥዮስ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋራ በዚህች ከተማ አንተ በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ለማሤር ተሰበሰቡ፤
“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤ አንተን የሚወድዱህ ግን፣ የንጋት ፀሓይ በኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።” ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።
አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ።”
ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ነጐድጓድና ዝናብ ላከ። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩ።
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጕቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
እግዚአብሔር ሳሙኤልን፣ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተ ልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፣ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ይሁን እንጂ በዚያ ዕለት እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ ስላንጐዳጐደባቸው እጅግ ተሸበሩ፤ ድልም ተመተው ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ።