ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ሁሉ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፥ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ።
ሶፎንያስ 1:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ሕዝብ ሁሉ እቀጣለሁ፤ ከዚያም ቦታ የበዓል አምልኮ ርዝራዥንና የጣዖት ካህናትን መታሰቢያ አጠፋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እጄን በይሁዳ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤ የበኣልን ትሩፍ፣ የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጄንም በይሁዳ ላይና በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፥ ከዚህም ስፍራ የበዓልን ትሩፍና የጣዖታቱን ካህናት ስም ከካህናቱ ጋር እቆርጣለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፣ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፥ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፥ |
ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ሁሉ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፥ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ።
ንጉሥ አካዝ ባሠራቸው መኖሪያ ክፍሎች ጣራ ላይ በሚገኘው ቤተ መንግሥት የይሁዳ ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን መሠዊያዎችና በቤተ መቅደሱ ሁለት አደባባዮች ንጉሥ ምናሴ አሠርቶአቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ኢዮስያስ ደመሰሳቸው፤ መሠዊያዎቹንም አንከታክቶ ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ ጣላቸው።
በእርሱም ትእዛዝ የእርሱ ሰዎች ባዓል ተብሎ የሚጠራው ጣዖት ይመለክባቸው የነበሩትን መሠዊያዎችንና በእነርሱም አጠገብ የነበሩትን ዕጣን የሚታጠንባቸውን መሠዊያዎች ሰባበሩ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎችንና ሌሎችንም ጣዖቶች ሁሉ ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ አደቀቁአቸው፤ ትቢያውንም ወስደው ለእነዚያ ጣዖቶች መሥዋዕት ያቀርቡ በነበሩ ሰዎች መቃብር ላይ በተኑት፤
ይህንንም በማድረጋችሁ ኀይሌን እገልጥላችኋለሁ፤ በምርኮኛነት ለሕዝቦች አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ዳግመኛ በሕዝብነት የማትታወቁ እስክትሆኑ ድረስ ጨርሼ አጠፋችኋለሁ፤ ከዚያ በኋላ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
በእርግጥም እጄን ዘርግቼ አገራቸውን አጠፋታለሁ፤ ከደቡባዊው በረሓ አንሥቶ በሰሜን በኩል እስከምትገኘው እስከ ሪብላ ከተማ ድረስ ባድማ አደርጋታለሁ፤ እስራኤላውያን የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ አንድም ሳይቀር አጠፋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንድ አሆንኩ ሰዎች ሁሉ ያውቃሉ።”
በሰማርያ ከተማ የሚኖሩ ሕዝቦች በቤትአዌን ስላለው በጥጃ ምስል በተሠራ ጣዖት በታላቅ ፍርሀት ይርበደበዳሉ፤ ክብሩ ስለ ተገፈፈ ሕዝቡ ያለቅሳሉ፤ የጣዖቱ ካህናትም እሪ ብለው ይጮኻሉ።
በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።