ሮሜ 13:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘመኑን በማስተዋል ይህን አድርጉ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ጊዜ አሁን ነው፤ መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን ወደ እኛ ቀርቧልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት ጊዜው አሁን መሆኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ አሁን መዳናችን ወደ እኛ ቀርቧልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእንቅልፍ የምትነቁበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዕወቁ፤ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እና ደርሳለችና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። |
የመርከብ አዛዡም ወደ እርሱ ቀርቦ “እንዴት ትተኛለህ? ኧረ እባክህ ተነሥና ወደ አምላክህ ጸልይ፤ ምናልባት ራርቶልን ሕይወታችንን ያድን ይሆናል” አለው።
ሲነጋ በጠዋት ደግሞ ‘ሰማዩ ደመና ሆኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ፤ የሰማዩንስ መልክ መለየት ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም።]
ይህ ሁሉ ነገር የደረሰባቸው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፤ የተጻፈውም በዘመናት መጨረሻ ላይ ለምንገኘው ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው።
ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።
አንዳንድ ሰዎች እንደሚመስላቸው ጌታ የተናገረውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም ሰው እንዳይጠፋ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሣል።
ልጆቼ ሆይ! ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ “የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል” ሲባል ሰምታችኋል፤ እነሆ፥ አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ በዚህ ምክንያት የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን።
ይህ ሁሉ የሚፈጸምበት ጊዜ ቅርብ ስለ ሆነ ይህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው! እንዲሁም የትንቢቱን ቃል የሚሰሙና በትንቢቱም ውስጥ የተጻፈውን የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።