መዝሙር 99:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደመና ዐምድ ሆኖ ተናገራቸው፤ የሰጣቸውንም ደንብና ድንጋጌ ፈጸሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤ እነርሱም ትእዛዙንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደመና ዓምድም ተናገራቸው፥ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ ግዙፍ በሆነ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ስለዚህም ሕዝቡ እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር በመስማት ከአሁን ጀምሮ አንተ የምትለውን ሁሉ ያምናሉ።” ሙሴም ሕዝቡ የሰጠውን መልስ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤
ሙሴም እጅግ ተቈጥቶ እግዚአብሔርን እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች የሚያቀርቡልህን መባ አትቀበል፤ እኔ ከእነርሱ አንዱን እንኳ አልበደልኩም፤ ሌላው ቀርቶ ከአህዮቻቸው አንዱን እንኳ አልወሰድኩም።”
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።