መዝሙር 97:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ፊት፥ ተራራዎች እንደ ሰም ይቀልጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት፣ በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራሮችም በጌታ ፊት፥ ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ። |
ይህም የሚሆነው ፈጣሪሽ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንደ ባልሽ ስለሚሆንና ‘የምድር ሁሉ አምላክ’ ተብሎ የሚጠራው የእስራኤል ቅዱስ አዳኝሽ ስለ ሆነ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ሂዱና ጠላቶቻችሁን እንደ እህል አበራዩ! ቀንዱ ብረት፥ ሰኮናው ነሐስ እንደ ሆነ በሬ ብርቱ አደርጋችኋለሁ፤ ብዙ መንግሥታትን ትደመስሳላችሁ፤ እነርሱ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለመላው ዓለም ጌታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አምጥታችሁ ታቀርባላችሁ።”
በእግዚአብሔር ፊት ተራራዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ ኰረብቶችም ይቀልጣሉ፤ በእግዚአብሔር ፊት ምድር ትናወጣለች፤ ዓለምና በውስጥዋ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ።
እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከታቸው ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፤ የጥንቱ ተራራዎች ይናዳሉ፤ ከጥንት ጀምሮ የእርሱ መረማመጃ የነበሩት ኰረብቶች ወደ ታች ይሰጥማሉ።
በቆሮንቶስ ከተማ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በውስጥዋም በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩት፥ እንደዚሁም በየቦታው ለእነርሱና ለእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለሚጠሩት ሁሉ።