ስለዚህ ብርቱ አደጋ አይደርስብህም፤ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይጠጋም።
ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤
ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
ቀንዴ አንድ ቀንድ እንዳለው ከፍ ከፍ ይላል፥ ሽምግልናዬም በዘይት ይለመልማል።
በድንኳንህ ሰላም እንደሚሰፍን ታረጋግጣለህ፤ የበጎችህንም በረት ስትጐበኝ ሁሉን በደኅና ታገኛቸዋለህ።
እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ሕይወትህንም በሰላም ይጠብቃል።
ደጋግ ሰዎች ምንም ክፉ ነገር አይገጥማቸውም፤ ክፉዎች ግን መከራ ይበዛባቸዋል። የሚያተርፉት ነገር የለም።
የማናየውን ነገር ተስፋ ካደረግን ግን በትዕግሥት እንጠባበቃለን።
እግዚአብሔር ከበሽታ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ በግብጽ አገር በነበርክ ጊዜ ካየኸው አሠቃቂ በሽታ ሁሉ ማንኛውንም በአንተ ላይ አያመጣም፤ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች በሚጠሉህ ላይ ያመጣባቸዋል።