መዝሙር 9:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችግረኞች ዘወትር እንደ ተረሱ አይቀሩም፤ የድኾችም ተስፋ ከንቱ ሆኖ ለዘለዓለም አይጠፋም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድኾችን ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤ የችግረኞችንም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም በሙሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሃ ለዘለዓለም የሚረሳ አይደለምና፥ ችግረኞችም ተስፋቸውን ለዘለዓለም አያጡም። |
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
ኢየሱስ ቀና ብሎ ወደ ደቀ መዛሙርቱ እየተመለከተ እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ናትና፥ እናንተ ድኾች የተባረካችሁ ናችሁ!
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?