መዝሙር 89:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ሆይ! የምስጋና መዝሙር የሚያቀርቡልህና በቸርነትህ ብርሃን የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እልልታን የሚያውቅ፣ በፊትህም ብርሃን የሚሄድ ሕዝብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ፥ ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከራን ባሳየኸን ዘመን ፋንታ፥ ክፉንም ባየንባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለናል። |
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
እነሆ መልካም ዜናን የሚያበሥር፥ ሰላምንም የሚያውጅ መልእክተኛ በተራሮች ላይ እየመጣ ነው። የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ክፉዎች ጠላቶችህ ፈጽሞ ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ ወዲህ አገርህን ከቶ አይወሩአትም! ስለዚህ ዓመት በዓሎችህን በደስታ አክብር! ስእለትህንም ለእግዚአብሔር ስጥ!
እንዲሁም በደስታ በዓሎቻችሁ፥ ማለት በወር መጀመሪያና በሌሎችም የተወሰኑ በዓሎቻችሁ፥ በሚቃጠል መሥዋዕትና በአንድነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶችን ትነፋላችሁ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ስለ እናንተ አስታዋሾች ይሆናሉ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
በእስራኤል ሕዝብ ላይ ክፉ አጋጣሚ ወይም ችግር እንደማይደርስባቸው ይታያል፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሥ መሆኑንም በይፋ ይናገራሉ።
አስተማሪዎች ካልተላኩስ እንዴት ቃሉን ሊያስተምሩ ይችላሉ? ይህም “የመልካም ዜና አብሣሪዎች መምጣት እንዴት ደስ ያሰኛል!” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
እስቲ ልጠይቅ፤ ታዲያ፥ ቃሉን አልሰሙም ማለት ነውን? በቅዱስ መጽሐፍ፥ “ድምፃቸው በዓለም ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ በእርግጥ ሰምተዋል።