መዝሙር 88:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርቱ ቊጣህ አደቀቀኝ፤ አስፈሪው ቅጣትህ ያጠፋኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤ መዓትህም አጠፋኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ከታናሽነቴ ችግረኛ ለሞትም የቀረብሁ ነኝ፥ በአስደንጋጭ ነገሮችህ ተሰቃየሁ፤ ምንም አቅም የለኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል፥ በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤ |
በእርሱ ላይ የተዛባ ፍርድ ተወስኖበት ተወሰደ፤ የወደፊትስ ሁኔታውን ማስተዋል የሚችል ማነው? ሆኖም ስለ ሕዝቤ መተላለፍ ተመታ፤ ከሕያዋንም ዓለም ተወገደ።
ከስድሳ ሁለት ሳምንት በኋላ መሲሑ ያለ ፍትሕ ይገደላል፤ የሚገደለውም ለራሱ አይደለም፤ የሚመጣው መሪ ወታደሮች ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን ይደመስሳሉ፤ መጨረሻውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ውድመት ስለ ታወጀ ጦርነት እስከ መጨረሻ ይቀጥላል።
“በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የሚሞት ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ ተረገመ ሰው ሆኖ ሕግ ከሚያስከትለው ርግማን ዋጀን።