መዝሙር 87:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! አስደናቂ ነገሮች ስለ አንቺ ተነግረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤ ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተከበረ ነገር ይባላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥ ሕይወቴም ለሞት ቀርባለችና። |
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ኢየሩሳሌምን ተመልከት! ሌሎች አገሮች በዙሪያዋ ሆነው በሕዝቦች መካከል እንድትሆን አድርጌአታለሁ፤
ከዚህ በኋላ እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ አየሁ፤ ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።