እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
መዝሙር 81:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥ የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣ አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም። |
እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
ሰማርያ የወደቀችበት ምክንያት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ነው፤ ይኸውም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አፈረሱ፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ በሆነው በሙሴ አማካይነት ለተሰጠ ሕግ ሁሉ ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ቃሉን ማዳመጥም ሆነ ሕጉን መጠበቅ አልፈለጉም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐመፀኞች ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እኔ ባላወጣሁላቸው ዕቅድ መመራት ይፈልጋሉ፤ ከእኔም ፈቃድ ውጪ የቃል ኪዳን ውል በመፈጸም በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራሉ።
የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን ለዘራፊና ለቀማኛ አሳልፎ የሰጠ ማነው? ይህን ያደረገው እግዚአብሔር ራሱ አይደለምን? ይህም የሆነው እኛ ስለ በደልነው፥ በሚፈቅደው መንገድ ስላልሄድንና ለሕጉም ታዛዦች ስላልሆንን ነው።
እነሆ ዛሬ እኔም መልሱን ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድነግራችሁ በእኔ አማካይነት ለላከላችሁ ቃል ሁሉ ታዛዦች አልሆናችሁም።
እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ ትኲረትም አልሰጡትም፤ በዚህ ፈንታ በእልኽና በክፋት የተሞላው ልባቸው የመራቸውን አደረጉ፤ ወደ ፊት ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ።
ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።
እግዚአብሔር ግን ተለያቸው። የሰማይንም ከዋክብት እንዲያመልኩ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም በነቢያት እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ ‘እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ! የታረደውን እንስሳና መሥዋዕትን አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ያቀረባችሁት ለእኔ ነውን?
ስለዚህ እርስ በርሳቸው በገዛ አካላቸው ላይ አሳፋሪ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ እግዚአብሔር ርኲሰት ለሞላበት ለክፉ ምኞታቸው ተገዢዎች እንዲሆኑ ተዋቸው።