በቀኝህ ያለውንና ለክብርህ ብርቱ ያደረግኸውን ጠብቀህ በሰላም አኑረው።
ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣ በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን።
በእሳት ተቃጥላለች ተነቅላማለች ከፊትህ ተግሣጽም የተነሣ ይጠፋሉ።
እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።
ይህችን አንተ የተከልካትን ተንከባክበህም ያሳደግኻትን የወይን ግንድ ጠብቃት!
እርሱን ለመርዳትና ለማበርታት፥ እኔ ዘወትር ከእርሱ ጋር ነኝ።
እርሱ ግን ተወግቶ የቈሰለው ስለ መተላለፋችን ነው፤ የደቀቀውም ስለ በደላችን ነው፤ እኛ የዳንነው እርሱ በተቀበለው ቅጣት ነው፤ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን።
አንድ ጊዜ እናንተ በፍሬ እንደ ተመላ የወይራ ዛፍ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንደ ነጐድጓድ የሚያስተጋባ ድምፅ በማሰማት ቅጠሉን በእሳት አቃጥላለሁ ቅርንጫፎችንም እሰባብራለሁ።
እንዲህም በላት! ‘እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ ሰይፉን ከሰገባው አውጥቼ ኃጢአተኛውንና ጻድቁን ከመካከልሽ አጠፋለሁ።