21 እርሱን ለመርዳትና ለማበርታት፥ እኔ ዘወትር ከእርሱ ጋር ነኝ።
21 እጄ ይደግፈዋል፤ ክንዴም ያበረታዋል።
21 አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፥ በቅዱስ ዘይቴም ቀባሁት።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
ሥልጣንህ እጅግ የበረታ ነው፤ ኀይልህም እጅግ ታላቅ ነው።
እኔ አምላካቸው አበረታቸዋለሁ እነርሱም ለቃሌ ይታዘዛሉ።” እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ።
ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።
እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤልም ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው።