በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
መዝሙር 80:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅርንጫፎችዋን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ዘረጋች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ ቍጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላደመጡኝም። |
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።
ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ከቲፍሳሕ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጐረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር።
ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት በሶርያ አገር እስከ ሐማት ግዛት አጠገብ በምትገኘው በጾባ ንጉሥ በሀዳድዔዜር ላይ አደጋ ጣለ፤ ይህንንም ያደረገው ሀዳድዔዜር ከላይ በኩል በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዘምቶ ስለ ነበር ነው፤
የምድርህንም ወሰን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳው እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ እንዲሰፋ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁ፤ ከፊትህም ታሳድዳቸዋለህ።