Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 23:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የምድርህንም ወሰን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳው እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ እንዲሰፋ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁ፤ ከፊትህም ታሳድዳቸዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “ድንበርህን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድረ በዳው እስከ ወንዙ ድረስ አደርገዋለሁ፤ በምድሪቱም ላይ የሚኖሩትን ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም አሳድደህ ከፊትህ ታስወጣቸዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ድንበርህንም ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረበዳ እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፥ ከፊትህ ታባርራቸዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 23:31
37 Referencias Cruzadas  

በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤


እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን፥ “አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደ ሆነ በእርግጥ ወደ አማልእክታቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ” ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፤ እነዚህን ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች እግዚአብሔር እንዳይጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፤ ሰሎሞን ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተሰባበረ።


በዚህን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር ‘ከቤንሀዳድ ሠራዊት ብዛት የተነሣ አትፍራ! እኔ ዛሬ በዚህ ሠራዊት ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርጋለሁ፤ አንተም ደግሞ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃለህ’ ይልሃል” አለው።


የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።


ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ከቲፍሳሕ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጐረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር።


በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር፤


ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤም ምድርና እስከ ግብጽ ግዛት ዳርቻ ድረስ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ያስገብር ነበር፤


ግዛቱ ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይድረስ።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሰው አትፍራው፤ በእርሱና በሕዝቡ በምድሪቱም ላይ ድል እንድትጐናጸፍ አደርግሃለሁ፤ በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ ያደረግኸውን ሁሉ በዚህም ላይ አድርግበት።”


“እስራኤላውያንን እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ወደ ከነዓን ምድር በምትገቡበት ጊዜ የርስታችሁ ወሰን እንደሚከተለው ይሆናል፦


ሰፈራችሁን ነቅላችሁ ወደ ተራራማው የአሞራውያን አገር፥ ወደ ጐረቤትም ወደ አራባ በደጋውና በቈላው አገር፥ በኔጌብ፥ በሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ በኩል፥ በከነዓናውያን አገርና በሊባኖስ በኩል አድርጋችሁ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።


እነሆ፥ ምድሪቱ በፊታችሁ ናት፤ እኔ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ላወርሳቸው የተስፋ ቃል የገባሁላቸውን ምድር ሄዳችሁ ውረሱ።’ ”


ስታልፉ በእግራችሁ የምትረግጡት መሬት ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም በደቡብ በኩል ካለው በረሓ ተነሥቶ በሰሜን በኩል እስካሉት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች፥ እንዲሁም በምሥራቅ በኩል ከሚገኘው ከኤፍራጥስ ወንዝ ተነሥቶ በምዕራብ በኩል እስከሚገኘው እስከ ታላቁ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሰፋል።


ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን በእኛ እጅ ስለ ጣለው እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ሰው ሁሉ ገደልን።


በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።


“እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር የሚገኙትን ከተማዎች በጦርነት በምትይዝበት ጊዜ ግን በውስጣቸው የሚገኘውን ሰው ሁሉ ግደል።


እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ ‘እርሱን አትፍራው፤ እርሱን ሕዝቡንና ምድሩን ሁሉ ለአንተ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ በሐሴቦን ተቀምጦ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ላይ እንዳደረግህ ሁሉ በዚህም ላይ አድርግበት።’


ይህንንም የምታደርገው ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ጠላቶችህን ሁሉ በማባረር ነው።


ነገር ግን እንደሚባላ እሳት የሆነ እግዚአብሔር አምላክህ በፊትህ የሚሄድ መሆኑን ዛሬ ታያለህ፤ አንተ ወደ ፊት በሄድህ መጠን እርሱ ድል ይነሣቸዋል፤ ስለዚህም እርሱ በሰጠው ተስፋ መሠረት እነርሱን ነቃቅለህ በማባረር በፍጥነት ታጠፋቸዋለህ።


ድንበራችሁ በስተደቡብ ካለው ምድረ በዳ ተነሥቶ በስተሰሜን እስከሚገኙት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች ድረስ፥ በስተምሥራቅ ከትልቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ፥ በመነሣት የሒታውያንን ምድር ሁሉ ጨምሮ በምዕራብ በኩል እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሆናል።


እናንተ ግን በዚያ አትቈዩ፤ ጠላትን እያሳደዳችሁ ከኋላ በኩል አደጋ መጣላችሁን ቀጥሉ፤ ሸሽተው ወደ ከተሞቻቸው እንዲገቡ መንገድ አትስጡአቸው! አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድልን ያቀዳጃችኋልና።”


እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራቸው፤ እኔ አንተን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ ከእነርሱ አንድም የሚቋቋምህ አይኖርም” አለው።


ከሊባኖስ እስከ ሚስረፎትማይም ድረስ በተራራማው አገር የሚኖሩ ነዋሪዎች፥ ማለት ሲዶናውያንን ሁሉ፥ እኔ ራሴ ከእስራኤላውያን ፊት አባርራቸዋለሁ፤ አንተ ግን እኔ እንዳዘዝኩህ ምድሪቱን ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ አከፋፍል።


ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ “የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ እኛን በመፍራት ሐሞታቸው ስለ ፈሰሰ በእውነት እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ ለእኛ አሳልፎ ሰጥቶአል።”


እግዚአብሔርም ለቀድሞ አባቶቻቸው በገባው ቃል መሠረት በአካባቢያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ብዙ ድልን አቀዳጅቶአቸው ስለ ነበረ ከጠላቶቻቸው አንድ እንኳ በፊታቸው ሊቆም አልቻለም።


“እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ደርሶአል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ያደረገላችሁን መልካም ነገር ሁሉ ከእናንተ እያንዳንዱ በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ ያውቃል፤ እርሱ ከሰጣችሁ ተስፋ አንድም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሞአል።


እናንተም የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ ወደ ኢያሪኮ መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ እንዲሁም አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን እናንተን ለመውጋት ተነሡ፤ እኔ ግን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኋችሁ።


በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ እንዳደረግሁት አስቀድሜ ከፊታችሁ ያባረራቸውን ተርብ ሰደድኩባቸው፤ ይህ በእናንተ ሰይፍ ወይም በእናንተ ቀስት የሆነ አይደለም።


እግዚአብሔር ሕዝቦችን እንዲሁም በምድሪቱ የሚኖሩትን አሞራውያንን ሁሉ ከፊታችን አባሮልናል፤ ስለዚህም እርሱ አምላካችን ስለ ሆነ እግዚአብሔርን እናመልካለን።”


ከዚህም በኋላ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወደሚኖሩት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ እነርሱ ተዋጉአችሁ፤ እኔ ግን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኋቸው፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው፤ ምድራቸውንም ወረሳችሁ።


ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን፦ “ጦርህን በዐይ ከተማ ላይ አንሣ፤ እኔ እርስዋን ለአንተ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር ወደ ከተማይቱ ዘረጋ።


በዚህን ጊዜ እናንተ ከተደበቃችሁበት ስፍራ ወጥታችሁ ከተማይቱን ያዙ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርም ከተማይቱን ለእናንተ አሳልፎ ይሰጣችኋል።


የእስራኤል ሰዎች ግን የገባዖንን ሰዎች “ከእናንተ ጋር እንዴት ውል እናደርጋለን? ምናልባትም እናንተ በእኛ መካከል የምትኖሩ ልትሆኑ ትችላላችሁ” አሉአቸው።


ከዚያ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ አብሮ ዘመተ። እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፈሪዛውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ እነርሱም በቤዜቅ ዐሥር ሺህ ሠራዊትን መቱ።


ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እስራኤላውያን በሠራዊቱ ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ። በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን በዚያ አገር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ወስደው የራሳቸው ርስት አደረጉት፤


ከዚህም የተነሣ ዳዊት እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “እኔ በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ስለማቀዳጅህ ሄደህ በቀዒላ ላይ አደጋ ጣል” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos