እነርሱም ከብንያም ነገድ ስለ ነበሩ የሳኦል ዘመዶች ነበሩ፤ እነርሱ በቀኝና በግራ እጃቸው ፍላጻ የመወርወርና ድንጋይ የመወንጨፍ ችሎታ ያላቸው ነበሩ፤
መዝሙር 78:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤፍሬም ልጆች ቀስትና ፍላጻ ይዘው ሳለ በጦርነት ቀን ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤፍሬም ልጆች የታጠቁ ቀስተኞች ቢሆኑም፣ በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬም ልጆች ለውጊያ ታጥቀው ቀስትንም ገትረው በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ፥ ርዳን፥ ስለ ስምህ ክብር አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኀጢአታችንን አስተስርይልን። |
እነርሱም ከብንያም ነገድ ስለ ነበሩ የሳኦል ዘመዶች ነበሩ፤ እነርሱ በቀኝና በግራ እጃቸው ፍላጻ የመወርወርና ድንጋይ የመወንጨፍ ችሎታ ያላቸው ነበሩ፤
በምልክቱም መሠረት በጦር ሜዳ የነበሩት እስራኤላውያን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ይወስዳሉ፤ እስከ አሁን ብንያማውያን ሠላሳ እስራኤላውያንን በመግደላቸው “ከዚህ በፊት እንዳደረግነው አሁንም ፈጀናቸው!” እያሉ ይደነፉ ነበር።
የዓቤድ ልጅ ጋዓልም እንዲህ አለ፦ “አቤሜሌክ ማን ነው? እኛ የሴኬም ሰዎች ለእርሱ የምንገዛው ለምንድነው? የጌዴዎን ልጅና የእርሱ የጦር መሪ ዜቡር የሐሞርን አባት ሴኬምን ያገለገሉ አይደሉምን? ለምን ለእርሱ እንታዘዛለን? ይልቅስ የጐሣችሁ መሥራች ለሆነው ለሴኬም አባት ለሐሞር ታማኞች ሁኑ።
ፍልስጥኤማውያንም በብርቱ ተዋግተው እስራኤላውያንን ድል ነሡ፤ እስራኤላውያንም ወደየድንኳናቸው ሸሹ፤ ታላቅ እልቂት ሆኖ ሠላሳ ሺህ እስራኤላውያን ወታደሮች ተገደሉ፤