የእግዚአብሔር ቊጣ በእነርሱ ላይ ተነሣ፤ የእስራኤልን ኀያላን ሰዎች ገደለ፤ ምርጥ ወጣቶችንም በአጭሩ ቀጨ።
የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው ላይ መጣ፤ ከመካከላቸውም ብርቱ ነን ባዮችን ገደለ፤ የእስራኤልንም አበባ ወጣቶች ቀጠፈ።
የእግዚአብሔር ቁጣ በላያቸው መጣ፥ ከእነርሱም ጠንካሮችን ገደለ፥ የእስራኤልንም ምርጦች መታ።
ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ በግዙፉ ሠራዊቱ ላይ የሚያመነምን በሽታ ይልክበታል፤ በሰውነቱም ውስጥ እንደ እሳት የሚያቃጥል ትኲሳት ይልክበታል።
የሚበሉት ሥጋ ገና በብዛት ሳለ፥ እግዚአብሔር በሕዝቡ እጅግ ተቈጣ፤ ብርቱ መቅሠፍትም በሕዝቡ መካከል አመጣ፤