መዝሙር 77:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሊቱን የማነጋው በጥልቅ ሐሳብ ነው፤ ሳሰላስል ሳለሁ ራሴን የምጠይቀው እንዲህ እያልኩ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ ከልቤም ጋራ ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዱሮውን ዘመን አሰብሁ፥ የጥንቱን ዓመታት አሰብሁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚመጣ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተውም ለልጆቻቸው ይነግራሉ። |
እኔማ በልቤ “ከእኔ በፊት ኢየሩሳሌምን ከገዙት ሁሉ ይበልጥ ታላቅና የጥበብ ሰው ሆኛለሁ፤ የጥበብንና የዕውቀትን ምንነት መርምሬ አጥንቻለሁ” ብዬ ነበር፤
“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።”
“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውን አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ እርሱም ይነግርሃል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ እነርሱም ይተርኩልሃል።