ሌሊቱን ሙሉ አነቃኸኝ፤ ጭንቀቴም ስለ በዛ መናገር አልቻልኩም።
ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤ መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።
እግዚአብሔርን ሳስታውስ እተክዛለሁ፥ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች።
የእግዚአብሔርን ምስጋና ተናገሩ፥ ኀይሉንና ያደረገውንም ተአምራት።
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ አጥቶ ስለ ነበር በቤተ መንግሥቱ መዝገብ ላይ የሰፈሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች አምጥተው ያነቡለት ዘንድ ትእዛዝ ሰጠ።
የሥቃዩንም ብዛት ስላዩ ምንም ቃል ሳይናገሩ ከእርሱ ጋር ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት በመሬት ላይ ተቀምጠው ሰነበቱ።
ከባሕር ዳር አሸዋ ይበልጥ በከበደ ነበር፤ ስለዚህ ትዕግሥት የጐደለው ንግግሬ ሊያስገርምህ አይገባም።
ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል።