ፍርድ ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፥ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፤
ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣምና፤
ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ፥ በእብሪተኛ አንገት አትናገሩ።
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ሁሉ አንቀላፉ።
የተዳፈረውም በትከሻው ላይ ጠንካራና ሰፊ ጋሻውን አንግቦ በትዕቢት ወደ እርሱ፥ እየገሠገሠ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤ ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ።
በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤ በዐይኑም መንግሥታትን አተኲሮ ያያል፤ ስለዚህ ዐመፀኞች በእርሱ ላይ ባይነሡ ይሻላቸዋል።
እኔ የእርስዋን ዕብሪተኛነት ዐውቃለሁ፤ ፉከራዋና ሥራዋ ከንቱ ናቸው።