መዝሙር 74:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተን የሚያምኑትን ነፍሶች ለአራዊት አሳልፈህ አትስጥ፤ የአገልጋዮችህንም ሥቃይ ለዘለዓለም አትርሳ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም የርግብህን ነፍስ አሳልፈህ ለዱር አራዊት አትስጥ፤ የችግረኞች ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለሙ አትርሳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትገዛልህን እርግብ ለአራዊት አትስጣት፥ የችግረኞችህን ነፍስ መቼውንም አትርሳ። |
አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤ እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ ድምፅሽ አስደሳች ነው፤ ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።
ፍቅሬ ሆይ! እንዴት ውብ ነሽ! እንዴት ያማርሽ ነሽ! ዐይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ያማሩ ናቸው፤ ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ ላይ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው።
እኔ ግን የምወደው አንዲትዋን ብቻ ነው፤ እርስዋም ምንም እንከን የሌለባት እንደ ርግብ የተዋበች ናት፤ እርስዋ ለእናትዋ አንድ ናት፤ የወለደቻት እናትዋም ከሁሉ አብልጣ ታፈቅራታለች፤ ቈነጃጅትም እርስዋን እየተመለከቱ ያወድሱአታል፤ ነገሥታትና የንጉሥ ቊባቶች ያሞግሡአታል።