የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቈይቶ ነበር፤ ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ፤
መዝሙር 72:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግዛቱ ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይድረስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይገዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይግዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐስበው ከንቱ ነገርን ተናገሩ። በአርያምም ዐመፃን ተናገሩ። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቈይቶ ነበር፤ ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ፤
የምድርህንም ወሰን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳው እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ እንዲሰፋ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁ፤ ከፊትህም ታሳድዳቸዋለህ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሠረገሎችን ከእስራኤል፥ የጦር ፈረሶችንም ከኢየሩሳሌም አስወግዳለሁ፤ የጦር ቀስቶችን እሰባብራለሁ፤ ንጉሥሽ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲኖር ያደርጋል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርና ከታላቁ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሆናል።”
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።