ንግሥተ ሳባ ያመጣችለትን ስጦታ ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን አበረከተችለት፤ ይኸውም ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፥ እጅግ ብዙ ሽቶና የከበረ ዕንቊ ነበር፤ እርስዋ ለሰሎሞን ያበረከተችው የሽቶ ብዛት ከዚያ በኋላ ከቀረበለት የሽቶ ገጸ በረከት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ነበር።
መዝሙር 72:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር! ከሳባ ወርቅ ይምጣለት፤ ስለ እርሱም ዘወትር ጸሎት ይደረግ፤ የእግዚአብሔርም በረከት ዘወትር ከእርሱ ጋር ይሁን! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜው ይርዘም! ወርቅም ከሳባ ይምጣለት፤ ዘወትር ይጸልዩለት፤ ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሐወት ይኑር፥ ከዓረብም ወርቅ ይሰጠው፥ ሁልጊዜም ስለ እርሱ ይጸልይ፥ ዘወትርም ይባረክ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር። |
ንግሥተ ሳባ ያመጣችለትን ስጦታ ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን አበረከተችለት፤ ይኸውም ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፥ እጅግ ብዙ ሽቶና የከበረ ዕንቊ ነበር፤ እርስዋ ለሰሎሞን ያበረከተችው የሽቶ ብዛት ከዚያ በኋላ ከቀረበለት የሽቶ ገጸ በረከት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ነበር።
ንግሥተ ሳባ ስለ ሰሎሞን የሚነገረውን አስደናቂ ጥበብ ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ የእንቆቅልሽ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፤ ወደ ኢየሩሳሌም ስትመጣም ብዙ የክብር አጃቢዎችን አስከትላ ሽቶ፥ የከበሩ ዕንቆችና እጅግ የበዛ ወርቅ በግመሎች አስጭና ነበር፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኘች ጊዜ በሐሳብዋ የነበረውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር ሆኖ አዩት፤ ተደፍተውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፥ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት።
ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።
ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።
ይህ ሕይወት ተገልጦአል፤ እኛም አይተነዋል፤ እንመሰክራለንም። በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለም ሕይወት እንነግራችኋለን።
እርሱ ብቻ መድኃኒታችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከጥንት ጀምሮ፥ አሁንም፥ ለዘለዓለምም ክብርና ግርማ፥ ኀይልና ሥልጣንም ይሁን! አሜን።