መዝሙር 71:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! መጥቼ ኀያል ሥራዎችህን ዐውጃለሁ፤ ትክክለኛ ፍርድ የመስጠት ኀይል የአንተ ብቻ መሆኑን እናገራለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥቼ የጌታ እግዚአብሔርን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ፤ የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ኃይል እገባለሁ፥ አቤቱ፥ ጽድቅህን ብቻ አስባለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራሮች ራስ ላይ ለምድር ሁሉ መጠጊያ ይሆናል፤ ፍሬውም ከሊባኖስ ዛፍ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፤ እንደ ምድር ሣር በከተማ ይበቅላል። |
ለእኛ ስላደረጋቸው ድርጊቶች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንደ መሐሪነቱ ስላሳየው ከፍተኛ በጎ አመለካከት፥ ስለ ተትረፈረፈውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምስጉን ድርጊቶቹን እዘረዝራለሁ።
ጻድቅ በእምነት ሕይወትን ያገኛል ተብሎ ተጽፎአል፤ የእግዚአብሔር ጽድቅም በሥራ ስለ ታየ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ሰው የሚጸድቀው በእምነት ነው።
ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።