Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 71:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 መጥቼ የጌታ እግዚአብሔርን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ፤ የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በጌታ ኃይል እገባለሁ፥ አቤቱ፥ ጽድቅህን ብቻ አስባለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! መጥቼ ኀያል ሥራዎችህን ዐውጃለሁ፤ ትክክለኛ ፍርድ የመስጠት ኀይል የአንተ ብቻ መሆኑን እናገራለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ለም​ድር ሁሉ መጠ​ጊያ ይሆ​ናል፤ ፍሬ​ውም ከሊ​ባ​ኖስ ዛፍ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፤ እንደ ምድር ሣር በከ​ተማ ይበ​ቅ​ላል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 71:16
23 Referencias Cruzadas  

ኀይልን በሚሰጠኝ በርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።


ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፣ ከእምነትም በሆነ ጽድቅ በርሱ ዘንድ እንድገኝ ነው።


የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤ አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል።


እግዚአብሔር ጻድቅ በመሆኑ መከራን ለሚያመጡባችሁ መከራን ይከፍላቸዋል፤


በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ።


በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤


በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፤ በስሙም ይመላለሳሉ” ይላል እግዚአብሔር።


አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ ቀኑን ሙሉ ያወራል፤ የእኔን መጐዳት የሚፈልጉ፣ ዐፍረዋልና፤ ተዋርደዋልም።


አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ ቀኑን ሙሉ ስለ ማዳንህ ይናገራል፤ ማቆሚያ ልኩንም አላውቅም።


እንግዲህ ልጄ ሆይ፤ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።


ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጽድቅ ስላላወቁና የራሳቸውን ጽድቅ ለመመሥረት ስለ ፈለጉ፣ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።


አሁን ግን ሕግና ነቢያት የመሰከሩለት፣ ከሕግ ውጭ የሆነ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጧል።


በወንጌል የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጧልና፤ ጽድቁም ከእምነት ወደ እምነት የሆነ ነው፤ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው።


ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።


የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ እግዚአብሔር ስላደረገልን ሁሉ፣ ስለሚመሰገንበት ሥራው፣ እንደ ፍቅሩና እንደ ቸርነቱ መጠን፣ ለእስራኤል ቤት ያደረገውን፣ አዎን፣ ስላደረገው መልካም ነገር እናገራለሁ።


እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።


እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ከአንተ ሌላ ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤ እኛ ግን የአንተን ስም ብቻ እናከብራለን።


ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል?


አምላክ ሆይ፤ ጽድቅህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ አንተ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤ አምላክ ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


በጽድቅህም ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።


የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሆናል፤ ኀይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios