መዝሙር 70:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ ግራም ይጋቡ፤ የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ፣ ይፈሩ፤ ይዋረዱም፤ ጕዳቴንም የሚሹ፣ ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አድነኝ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጽድቅህ አስጥለኝ፥ ታደገኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ፈጥነህም አድነኝ። |
በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።
እግዚአብሔር ፊደል በፊደል ላይ፥ መስመር በመስመር ላይ፥ ትምህርት በትምህርት ላይ እያነባበረ ሊያስተምራችሁ የፈቀደው ስለዚህ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርምጃችሁ ሁሉ ትሰናከላላችሁ፤ ትቈስላላችሁ፤ በወጥመድም ተይዛችሁ ትታሰራላችሁ።