መዝሙር 7:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሌሎች ወጥመድ የሚሆን ጥልቅ ጒድጓድ ይቈፍራሉ፤ ነገር ግን በቈፈሩት ጒድጓድ ውስጥ እነርሱ ራሳቸው ይገቡበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕድጓድ ምሶ ዐፈሩን የሚያወጣ፣ በአዘጋጀው ጕድጓድ ራሱ ይገባበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ክፋትን ያማጠ ተንኮልን ፀነሰ፥ ውሸትንም ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕድጓድንም ማሰ፥ ቈፈረም። ባደረገውም ጕድጓድ ይወድቃል። |
ጠላቶቼ እኔን ለመያዝ ወጥመድ ዘርግተውብኛል፤ ሁለንተናዬን የሚያጐብጥ ተስፋ መቊረጥ ደረሰብኝ፤ በመንገዴ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ወደቁበት።
ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።
ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ።
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ በየአገሩ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች በጽሑፍ እንዲህ የሚል መልእክት አስተላለፈ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!