10 እኔ ያለ ጒዳት ሳልፍ ክፉዎች ባጠመዱት ወጥመድ ይያዙ።
10 እኔ ብቻ በደኅና ሳመልጥ፣ ክፉዎቹ በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ።
10 እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ክፉዎች በወጥመዳቸው ይውደቁ።
ያላሰቡት ድንገተኛ ጥፋት ይድረስባቸው፤ የደበቁት ወጥመድ ይያዛቸው በቈፈሩትም ጒድጓድ ወድቀው ይጥፉ!
የከበቡኝ ጠላቶቼ በእኔ ላይ ያቀዱትን ሤራ በእነርሱ ላይ እንዲፈጸም አድርግ።
ስለዚህም ሃማን መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ፤ ከዚያም በኋላ የንጉሡ ቊጣ በረደ።
ጻድቅ ከመከራ ይድናል። መከራው ግን በክፉ ሰው ላይ ይደርሳል።